Skip to main content
plan01
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ ተምሳሌት ነው:- አቶ አገኘሁ ተሻገር የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ
(ሆሳዕና፣ህዳር 29/2018)የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በዛሬው እለት የተከበረውን 20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት ከክልሉ እና ከፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል።
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በምክክር መድረኩ እንደገለጹት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ከፍ ባለ ደረጃ እንዲከበር አድርጓል ብለዋል።
ከክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ይህን ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮ በቁርጠኝነት መወጣት ችለዋል ሲሉም አፈ ጉባኤው አብራርተዋል።
የክልሉ መንግስት ለበዓሉ ልዩ ትኩረት በመስጠት አስቀድሞ ዝግጅት በማድረጉ ሀገራዊ አጀንዳው ስኬታማ እንደነበር በአብነት ጠቅሰዋል።
በክልሉ ከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ እና ሌሎች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እንደነበርም አስረድተዋል።
ክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ ተምሳሌት ስለመሆኑም አቶ አገኘሁ በንግግራቸው አመላክተዋል።
በዓሉ የክልሉን ጸጋዎች እና የመልማት ዓቅም በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ትርጉም እንደነበረውም አፈ ጉባኤው በአብነት ጠቅሰዋል።
የክልሉ ህዝብ የላቀ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ጎልቶ የታየበት በዓል ስለመሆኑም አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተናግረዋል።
ህዝቡ ላደረገው ደማቅ አቀባበል አፈ ጉባኤው ምስጋና አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት በዓሉ ስኬታማ እንዲሆን ከፌደሬሽን ምክር ቤት ጋር በቅንጅት መስራት መቻሉን ተናግረዋል።
የመላው ኢትዮጵያውያን በዓል መሆኑን ተከትሎ ለዘርፉ የተሰጠው ልዩ ትኩረት እና የአመራር ቁርጠኝነት ከፍተኛ እንደነበርም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በዓሉን ለማክበር አስቀድሞ ጠንካራ እቅድ መዘጋጀቱን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና የገጽታ ግንባታ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ህብረ ብሔራዊነት ጎልቶ የታየበት በዓል እንደነበር የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ለክልሉ ተደማሪ አቅም እንደሚፈጥርም አስረድተዋል።
በክልሉ በተለያዩ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የሚከበሩ በዓላት ካላቸው ፋይዳ አንጻር የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል።
በዓላቱ የህዝብን አቅም በማላቅ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ላይ የሚኖራቸውን አበርክቶ ከፍ ለማድረግ እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።