Skip to main content
later
የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፕላንና ልማት ቢሮ ዕቅድ አፈጻጸምን ገመገመ
(ሆሳዕና፦ጥር 18/2018 ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፕላንና ልማት ቢሮ የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል።
የምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ እንደገለፁት የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ክልላዊ ሀብት ማከፋፈያ ቀመር አሰራር እና ክልላዊ ልማት ዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ቢሮው የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ መረጃዎችን በማደራጀት፣በመተንተን ብሎም በማሰራጨት አኳያ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የክልሉን ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትልና የልማት መረጃና ስነ ህዝብ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ፈለቀች ተ/ማሪያም እንደገለፁት የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ክፍፍል አሰራርን በማዘመን ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በቀመር አሰራርና አዘገጃጀት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግልፀኝነትና ከመፍጠር ረገድ ሰፊ ስራዎች ተሰርቷል።
ክልላዊ የልማት ዕቅድ ዝግጅት የዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ስራዎች ላይ ለፈጻሚዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የህዝብ ቁጥር ዕድገት ምጣኔው ከክልሉ ኢኮኖሚ ልማት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የማከናወን ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለው በመረጃዎች ጥራት የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት ይሰራል።
በአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሚታየውን የዕቅድና ሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት ክፍተቶችን ለመሙላት ለፈጻሚዎች ስልጠናዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ4 ተከታታይ ቀናት በወልቂጤ ከተማ በቋሚ ኮሚቴዎች ሲገመገም የቆየው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ግምገማ ተጠናቋል።