Skip to main content
jvnb

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሆሳዕና ክላስተር በቁጥር ሁለት ህብረት የፍኖተ ፕላን ቤተሰብ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፓርቲ ተግባር አፈፃፀምን አባላት ተገመገሙ።

ታህሣስ 29/2018 /ዓ.ም ሆሳዕና ። በጉባኤው ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ስራዎች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ ልምዶች በዝርዝር ተገምግሟል ። በአፈጻጸም ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን ማሻሻል ተገቢ እንደሆነም በመድረኩ ላይ ተገልጿል ። በቀሪ ወራት የአመቱን እቅድ ለማሳካት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የቤተሰቡ አባለት ሰብሳቢ አቶ ታደለ ተገሰ አቅጣጫ አስቀምጧሉ ።

አባላት የፖርቲና የመንግሥት ሥራ አፈፃፀምን በተሻለ ሁኔታ መፈፀም ፣ ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማሻሻል እና ተጠያቂነትን ማጎልበት ላይ ትኩረት ተሰጥተዋል። እንዲሁም ለሚቀጥሉት 6 ወራት የስራ አቅጣጫና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ተወስነው ፥ እቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት አፅኖት ተሰጥቶበት ዉይይት ተደርጎባቸዋል ።

ጉባኤው በአባላት የተጠናከረ ቁርጠኝነት፣ በተሻለ የመፈጸም አቅም ለመስራት ቃል በመግባት እና በተገኘው ውጤት ባለመዘናጋት በቀሪው ግማሽ ዓመት የተሻለ ዉጤት ለማምጣት የጋራ ግብ በማስቀመጥ የተጠናቀቀ ሲሆን በመጨረሻም የአባላት ምዘና ተካሄዶ ተጠናቋል ።

ለበጠ መረጃ :-Facebook =https://www.facebook.com/profile.php?id=61584419631289

Website =Www.cerbopd.gov.et

whatsapp=https://whatsapp.com/channel/0029VbCPHMm5q08lHnZppt2F

Telegram=https://t.me/CenteralEth

Twitter =https://x.com/Plan166088

Tiktok=https://vt.tiktok.com/ZSapqbHtj/

ይጎበኙ ።