Skip to main content
Al

ብልፅግና ፓርቲ ታሪክን ወደ ሀብት፥ ቅርስን ወደ እሴት የቀየረ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክትን ዛሬ ይፋ አድርገናል።

ፓርቲያችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ይሁንታ በማሸነፍ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሻገር ዋንኛ  ግባችን ነዉ፡፡

በዚህም መሠረት የፓርቲያችን የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ነዉ ። ምልክቱም የመደመር፣ የትብብር እና የአንድነት ምልክት ማሳያ ነው፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ከስድስተኛው ምርጫ በኋላ በኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዘርፎች ላይ ባከናወናቸው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ለውጦች ውስጥ ትገኛለች።

በዲጂታል ኢትዮጵያ ፣ በዲጂታል ፋይናንስ፣ በዲጂታል አገልግሎት እንዲሁም ሀገሪቱን ከዕዳ ወደ ምንዳ የማሻገር ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በማኅበራዊ መስተጋብሮች በሕዝቦች መካከል ትሥሥር ለመፍጠር ሕዝባዊ እና ባህላዊ በዓላትን እንዲጠናከሩ ተደርገዋል።

ይህም ኢትዮጵያ አቀርቅራ እንደማትቀር አሳይቷል፣ ታሪክም ተቀይሯል።

ለብልፅግና ፓርቲ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው መንግሥት መገንባት፣ በተለያዩ አካባቢ የሚታዩ ግጭቶችን መፍታት፣ የኢትዮጵያ የተጽዕኖ አድማስ ማስፋት እንዲሁም የዴሞክራሲ ፖለቲካን ባህል መገንባት የቀጣይ ጊዜያት ዋንኛ ዕቅዶቻችን ናቸው፡፡
ለበጠ መረጃ :-Facebook =https://www.facebook.com/profile.php?id=61584419631289
Website =Www.cerbopd.gov.et
whatsapp=https://whatsapp.com/channel/0029VbCPHMm5q08lHnZppt2F
Telegram=https://t.me/CenteralEth
Twitter =https://x.com/Plan166088
Tiktok=https://vt.tiktok.com/ZSapqbHtj/
ይጎበኙ ።