Skip to main content
gg

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" የሚለው መሪ ቃል የብልጽግናችን ትልቁ ግብ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሻገር መሆኑን ማሳያ ነው ለዚህ ግብ ሀላፊነታችንን እንወጣለን፦ አቶ አክሊሉ መኔዶ

ሆሳዕና የካቲት 06/2018 ዓ.ም

''ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር "በሚል መርህ ቃል የሆሳዕና ክላስተር ብልጽግና ህብረት ቁጥር-2 የ2ኛ ሩብ አመት የአባላት ኮንፈረንስ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሂዷል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆሳዕና ክላስተር የብልጽግና ህብረት ቁጥር -2 ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ መኔዶ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" የሚለው መሪ ቃል የብልጽግናችን ትልቁ ግብ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሻገር መሆኑን ማሳያ ነው ለዚህ ግብ ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

7ተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄደው በልዩነት ፍጹም ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ፣ፍትሃዊ ተዓማኒ ሆኖ፣በህዝብ ዘንድ ታላቅ ቅቡልነት የሚታይ እንዲሆን ሁሉም ድርሻቸውን ወስደው እንዲሰሩ አቶ አክሊሉ አሳስበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በመሪነቱ ሀገራዊ ልማት ለማረጋገጥ የገባውን ሀገራዊ ቃል በተግባር እየፈፀመ ለቀጣይም ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያለው ራዕይ ለማሳከት ፅኑ እምነት ያለው ፓርቲ ነው ሲሉም አንስተዋል።

በዚህም በቀጣይነት የመራጮች ምዝገባን በብቃት ማጠናቀቅ ፣የምርጫ ሕግና ሥነ_ምግባርን ማክበር እንዲሁም የመደመር፣ የትብብር እና የአንድነት ምልክት ማሳያ የምርታማነት መግለጫ የሆነውን ''የስንዴ ነዶ''የምርጫ ምልክት ለሕዝብ ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አሳስበዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆሳዕና ክላስተር የብልጽግና ህብረት ቁጥር-2 የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ አያሌው ዝና በመድረኩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም ለቀጣይ ትልቁ ተልዕኳችን በቁርጠኝነት ለመፈጸም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የሆሳዕና ክላስተር የብልጽግና ህብረት ቁጥር-2 ያለፉት ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ መንግስት የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የልማት መረጃ አስተዳደርና ስነ ህዝብ ጉዳዩች ዘርፍ ኃላፊ እና የህብረቱ አደረጃጀት ዘርፍ ዶክተር ፈለቀች ተ/ማሪያም ቀርቧል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የህብረቱ የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን ም/ሰብሳቢ አቶ ሽመል ዋንጎሬ የኮሚሽኑን ያለፉት ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

የህብረቱ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙርሳል አማን አጠቃላይ የምርጫ ሂደት፡የፓርቲያችን የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ”ን በማስመልከት ለአባላቱ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

በማጠቃለያው የዕጩነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ አባላት በማጽደቅ፥በቀረቡ ሰነዶች መነሻ ከአባላቱ ውይይት የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ የምርጫ ሂደት በማስመልከት ለአባላቱ ግንዛቤ በመፍጠር በኮንፍረንሱ ላይ አቋም ተይዞ መድረኩ ተጠናቋል።