AdminPlan
በመደመር መንግስት እሳቤ የዜጎቻችንን ኑሮ እና ህይወት ለማሻሻል ከተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክፕሮጀክቶቻችንቶቻችን አንዱ የገጠር ኮሪደር ልማት ነው፡፡
ዘመኑን የዋጁና ነገን ታሳቢ ያደረጉ ከተሞችን ለመፍጠር እየሰራን ያለነው ስራ ገጠሩን ያገለለ እንዳልሆነ ይህ ፕሮጀክት የገጠር መንደሮችን እያሻገረ እማኝ ሆኗል፡፡
ዛሬም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መስርያ ቤታችን ከተጠሪ ተቋማቶቻችን ጋር በመሆን በሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ ያስገነባውን ሞዴል የገጠር ኮሪደር መንደር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልል አመራሮች ጋር በመሆን አስመርቀናል።
ሞዴል መንደሩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን የተሰራ ሲሆን ዘመናዊ መኖርያ እና በዘላቂነት ህይወታቸውን የሚደግፉበት የሌማት ትሩፋት የተሟላለት ለእያንዳዳቸው የእንስሳየእንስሳትት ማደርያ እእናና የወተት ላሞች የዶር ቤትና ጫጩቶች እንዲሁም የንብ ማነብያ ባህላዊና ዘመናዊ ቀፎዎችን ያሟላ ነው፡፡



