የፕላንና ልማት ቢሮ የመካከለኛ ዘመን (2019_2021) የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ዝግጅት እና በፕሮግራም በጀት ዝግጅትና አስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ፡፡
ሆሳዕ ሴኔ /2018 ዓ.ም (የፕ.ል.ቢሮ )
ስልጠና ዋነኛ ትኩረቱ ከ2019 ዓ.ም እስከ 2021 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የሚተገበረውን የመካከለኛ ዘመን የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ዝግጅት እና በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ላይ ሰነድ ቀርቦ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል ።
በስልጠና መድረኩ የተገኙት የማክሮ ኢ/ዕ/ዝ/ክ/ግ/ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙባረክ አወል እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በክልላችን የለውጡን እንቅስቃሴ ተከትሎ በልዩ ሁኔታ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ ከሚደረግባቸው ተቋማት መካከል ቢሮው አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የፕሮግራም በጀት ስርአት በተሟላ እውቀትና ክህሎት በመምራት እንዲተገበር የስልጠና መድረኩ ያግዛል ብለዋል።
የፕሮግራም በጀት ስርዓት ዋነኛ ዓላማ ያለን ውስን በጀት በውጤት ላይ እንዲመሰረት በማድረግ የልማት ዕቅድ ከበጀት ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም የመደበኛ ወጪን ከካፒታል ወጪዎች ጋር በማስተሳሰር ተፈፃሚ የሚያደርግ ነው።
የመካከለኛ ዘመን (2019_2021) የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ዝግጅት ሰነድ በፕላንና ልማት ቢሮ የልማት ፕሮግራሞቾ
ች ባለሙያ አቶ ታምራት ዓለሙ አቅርበዋል እንዲሁም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚዘጋጀውን የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ በአቶ ተከተል ዮሴፍ የተለያዩ ዕቅድ ፎርማት ቀርቦ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
በስልጠናው የቢሮ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የሁሉም ስራ ሂደቶች ዳይሬክቶሬቶች፣ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም በአጠቃላይ የቢሮውን ፕሮግራም በጀቲንግ የሚያዘጋጁ የቴክኒክ ኮሚቴ በቀጣይ ጊዜ ለማደራጀት አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ የግንዛቤ ስልጠና ተጠናቋል።
የዘገበው የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ነው። See less


