Skip to main content
dul;l

የክልሉ መስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ

(ሆሳዕና፣ ሐምሌ 4/2018)፤ 42ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳደር ምክርቤት በክልሉ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የእቅድ አፈጻጸም በሁሉም የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሰላምና ፀጥታ እና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች ውጤታማና አበረታች እንደነበር በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዓመታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሁኔታን በተመለከተ፣ ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ወይም የኢኮኖሚ ዕድገት በ10.2 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።

ጠቅላላ የክልሉ ዓመታዊ ምርትን በየክፍላተ ኢኮኖሚው አስመልክቶ በግብርናው ዘርፍ 8.1 በመቶ እድገት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ ተመልክቷል።

በኢንዱስትሪው ዘርፍ 21.8 በመቶ እድገት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን በአገልግሎት ዘርፍ 10.5 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል።

በግብርናው ዘርፍ የታረሰ መሬት አድጓል፣ የሰብል ምርትና ምርታማነት አድጓል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን መጨመሩ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ ዕድገትም መጨመሩ ተመላክቷል።