AdminPlan
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፕላንና ልማት ቢሮ የቀድሞ አመራሮች አዲስ ከተሾሙት አመራሮች ጋር የትውውቅና የስራ ርክብክብ አደረጉ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የቀድሞ የስራ ኃላፊዎች አዲስ ከተሾሙት አመራሮች ጋር የትውውቅና የስራ ርክብክብ አድርገዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በቅርቡ የአመራር ምደባና ሽግሽግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ዳንኤል ዳምጠው የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑ ሲሆን የቀድሞ የተቋሙ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
እንዲሁም በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ ምክትል ኃላፊና የልማት መረጃ አስተዳደርና የስነ ህዝብ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ፈለቀች ተ/ማሪያም ከቀድሞ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዓለሙ ጋር የስራ ርክብክብ አድርገዋል:: በመርሀ-ግብሩ የቀድሞ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ ለአዲስ አመራሮች ተቋሙ የሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ለተደረገላቸው ገለፃና አቀባበል አመስግነው በተቋሙ የተሰሩ ውጤታማ ተግባራት በመቀናጀት ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል።
በመድረኩ የፕላንና ልማት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ለተቋሙ አዲስ አመራሮች አቀባበልና ለቀድሞ አመራሮች የሽኝት መርሀግብር በማካሄድ ለቀድሞ አመራሮችና አዲስ ለተሾሙት አመራሮች መልካም የሥራ ጊዜን ተመኝተዋል።