Skip to main content
news3

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በተገኙበት በፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) የተመራዉ ልዑክ ከክልሉ አመራሮች ጋር ዉይይት እያደረገ ይገኛል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በተገኙበት በፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) የተመራዉ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዉይይት እያደረገ ይገኛል። ዉይይቱ በልማት ዕቅድ አዘገጃጀት፣አተገባበርና አስተዳደር ፣ በፕሮጀክቶች ዕቅድ፣ አስተዳደርና አመራር፣ በመረጃ አደረጃጀት፣ አስተዳደርና አጠቃቀምና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ስለ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመስራረት፣ እና ከምስረታዉ በኋላ በነበረዉ የሽግግር ሂደት ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳራቶችን በተመለከተ አጭር ገለፃ አድርገዋል። ክልሉን የማደራጀቱ እና የማጠናከሩ ሂደት ከቀድሞዉ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በተሻገረ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ እና በሌሎችም ችግሮች የተፈተነ መሆኑን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣ በተለይም ከዕዳው መካከል 80 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ተመላሽ መደረጉን አንስተዋል። ክልሉ የብዝሃ ከተማ አቅጣጫን የሚከተልና ሰባት የክልል መቀመጫ ማዕላት ያሉት መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። ክልሉ ልዩ ልዩ ባህሪ ያላቸዉ አሰቸጋሪ ሁኔታዎችን እየፈታና እየተሻገረ ነባር ፕሮጀክቶችን እያጠናቀቀ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ደግሞ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል ፣ በዚህም መሠረት በሰባቱም የክልል ማዕከላት የቢሮዎች ሕንፃ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል ። በክልሉ ልዩ የሰላምና ፀጥታ ግንባታ፣ ግብር ልማት ፣ ገቢ ሴክተር ፣ የትምህርት ልማት፣ ፣ጤና ፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንቨስትመንት፣ ንግድና ገበያ ልማት ፣ መሠረተ ልማትና መሰል ጉዳዮች ላይ በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል። ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር ) እንደገለፁት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸዉ ለክልሎች ድጋፍና ክትትልን በማጠናከር የአንድ ዕቅድ፣ የአንድ ሪፖርት ስዓትን ለማጠናከር የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። መረጃ መር ውሳኔ ከመስጠት፣ ከልማት ዕቅድ ዝግጅትና አስተዳደር ፣ ፕሮጀክቶችን ከማቀድ፣ ከመተግበርና ከማስተዳደር አንፃር መድረኩ ተጫማሪ አቅም ይሆናል ማለታቸውን ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።